Fana: At a Speed of Life!

በመጪው ምርጫ የሴቶችና የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና አረጋውያንን ተሳትፎ ትርጉም ባለው ደረጃ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው አሉ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፡፡ በሴቶችና ወጣቶች የምርጫ ተሳትፎና በማህበራዊ…

በግንባታ ላይ የሚገኙ የአውሮፕላን ማረፊያዎችን ለማጠናቀቅ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በተለያዩ አካባቢዎች በግንባታ ላይ የሚገኙ የአውሮፕላን ማረፊያዎችን ለማጠናቀቅ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው አለ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን፡፡ በባለሥልጣኑ የኤሮድሮም ሴፍቲና ስታንዳርድ ዳይሬክተር ምስራቅ ጥላሁን ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷…

ኢጋድ ሱዳን በድርጅቱ ሙሉ ተሳትፎዋን ለመቀጠል ያሳለፈችውን ውሳኔ በደስታ ተቀበለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሱዳን ሪፐብሊክ በድርጅቱ ሙሉ ተሳትፎዋን ለመቀጠል ያሳለፈችውን ውሳኔ በደስታ ይቀበላል አለ። የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ የሱዳን ወደ ኢጋድ የመመለስ…

ለኢትዮጵያ እድገት ወሳኝ የሆነው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ሚና የጎላ ነው አሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ። በሳዑዲ አረቢያ እና በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ትብብር የተዘጋጀውና በፍጥነት በማደግ ላይ ባሉ…

በአዋሽ ባንክ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት የ1 ትሪሊየን ብር ክፍያ ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት 6 ወራት በአዋሽ ባንክ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት የተከናወነው የክፍያ መጠን አንድ ትሪሊየን ብር ደረሰ። ባንኩ ከዛሬ ጀምሮ "ለላቀ የደንበኞች እርካታ እንተጋለን" በሚል መሪ ሐሳብ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የደንበኞች ሳምንት ያካሂዳል።…

በእግር ኳስ ሕይወቱ 13ኛ ክለቡን የተቀላቀለው ሮድሪጌዝ…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ2014 የብራዚል ዓለም ዋንጫ በኋላ በምርጥ ብቃቱ መቀጠል ያልቻለ ተጫዋች ነው ኮሎምቢያዊው የፊት መሾመር ተጫዋች ሀሜስ ሮድሪጌዝ፡፡ በፈረንጆቹ 1991 የተወለደው ሀሜስ ሮድሪጌዝ እግር ኳስን መጫወት የጀመረው በሀገሩ ክለብ ኢንቪጋዶ ነው፡፡…

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቅድመና ድህረ ወሊድ አገልግሎት መጠናከር በጤና ተቋም የሚወልዱ እናቶችን ቁጥር አሳድጓል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቅድመ ወሊድና ድህረ ወሊድ አገልግሎት መጠናከር በጤና ተቋም የሚወልዱ እናቶችን ቁጥር አሳድጓል አለ የክልሉ ጤና ቢሮ። "ፈጠራና ዘላቂ ፋይናንስ ለጤናማ እናትነት" በሚል መሪ ሀሳብ የጤናማ እናትነት ወር በክልሉ ቡታጅራ…

በ24 ሰዓት የሥራ ባሕል የመዲናዋ የኮሪደር ልማት ሼል እየተፋጠነ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ የ24 ሰዓት የሥራ ባሕል የኮሪደር ልማት ሼል በፍጥነት እየተከናወነ ነው አሉ፡፡ ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ በኮሪደር ልማት ሾል ሳምንቱን ሙሉ ለ24…

ከ27 ሺህ በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች …

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደሀንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በስድስት ወራት ከተሞከሩ 27 ሺህ 773 የሳይበር ጥቃቶች 99 ነጥብ 03 በመቶ የሚሆነውን ማክሸፍ ተችሏል አለ። ተቋሙ የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል።…

በአማራ ክልል በጤና ጣቢያዎች የሚሰጠውን የእናቶች ህክምና አገልግሎት ለማሻሻል እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ውስጥ የሚሰጠውን የእናቶች ህክምና አገልግሎት ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ ነው አለ። ቢሮው “ፈጠራና ዘላቂ ፋይናንስ ለጤናማ እናትነት” በሚል መሪ ሀሳብ የተከበረውን ጤናማ የእናትነት ወር…